Metsihafe Sinksar Pro መጽሐፈ ስንክሳር 1.0

3

Pro hodnocení programu se prosím nejprve přihlaste

Staženo
2 ×
መጽሐፈ ስንክሳር አስተጋብአ (ሰበሰበ) ከለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን አስተጉቡእ (ስብስብ) ማለት ነው ፡፡ ጥርቅምቅም ውጥንቅጥ የተቀያየጠ መድበል የተደባበለ ነገር ማለት ነው ።

የሥላሴን አንድነትና ሦሥትነት÷ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ቅድመ ዓለም ያለእናት ከበሕርይ አባቱ ከአብ÷ ድኅረ ዓለም ያለአባት ከእመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ መወሐዱን÷ የመላእክትን ማዕርግና ሹመት የሚያስረዳ የነቢያትንና የሐዋሪያትን የጻድቃንንና የሰማዕታትን የደናግልንና የመነኮሳትን ምግባር መከራና እረፍት ከዕለት እስከ ዓመት የሚነገር መጽሐፍ ነው፡፡ የቤተ ክሲያንን ታሪክ÷ የመቤታችንን ዜና የልጇንም በጎ ሥራ ኹሉ በሰፊው ይናገራል። ትርጓሜውም በጽርእ የተሰብሰበ ስብስብ ማለት ነው። የቅዱሳን ነቢያትንና ሐዋርያትን÷ የቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታትን÷ ሀይማኖታዊ ተጋድሎ÷ ክርስቲያናዊ ፅናትና ግብር በአጠቃላይ ገቢረ ተአምራታቸውን÷ ገድላቸወንና ትሩፋታቸውን የሚዘክር ዕለተ መታሰቢየቸውንም የሚጽሐፍ መጽሐፍ ነው፡፡ ጠቅለል ባለ ቋንቋ መጽሐፈ ስንክሳር ዝክረ ቅዱሳን መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፈ ስንክሳር ከመጻሕፍተ ብሉያትና ሐዲሳት÷ ከገድላትና ድርሳናት የተቀዳ በቤተ ክርስቲያን በየቀኑ የሚነበብ ዜና ቅዱሳን ነዉ፡፡



የመጽሐፉ ስም ከዓመት እስከ ዓመት የሚነበብ የቅዱሳን ዜና ከየገድላቸው ባጭር ባጭር ቃል የተሰበሰበ እሉድ ምእላድ እስትጉቡእ ማለት ነው፡፡

እስከ ዓመት በአሉት ዕለታት የሞቱ የነቢያትን የሐዋርያትን የሰማዕታትን የጻድቃንን የመነኮሳት የደናግል በእግዚአብሔር ስም ለዐረፉ ታሪካቸውና ገድላቸው የተጻፈበት ወይም የሞቱበትንም ቀን የሚዐሳስብቀ መጽሐፈ ስንክሳር መድበል።
  • Verze programu

    1.0

  • Poslední aktualizace od vývojáře

    31. 7. 2019

  • Počet stažení za měsíc

    2 ×

  • Velikost

    7,8 MB

  • Potřeba instalace:

    Ne

  • Web autora

    Goranda Systems

Zobrazit více
Přejít do Google Play
Cena: 139,99 Kč

Sdílet

TIP: Stahují se vám programy pomalu? Změřte si rychlost svého internetového připojení.